ጋዜጣዊ መግለጫ
እናት ባንክ ለተለያዩ የብድር ዘርፎች የብድር ወለድ ስረዛና የአገልግሎት ማሻሻያ አደረገ
ግንቦት 4, 2012 ዓ. ም – አዲስ አበባ ኢትዮጵያ፡ ኮረና ቫይረስ በወረርሽኝነት በአለምአቀፍ ደረጃ መሰራጨት ከጀመረበት ወቅት አንስቶ በአለም ማህበረሰብ ላይ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውሶችን በማድረስ ላይ ይገኛል ፡፡ በአገራችንም በተለይ በኢኮኖሚው ዘርፍ ይኸውም በአጠቃላይ የንግድ እንቅስቃሴውና በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት በማድረስ ላይ ነው፡፡
እናት ባንክ ይህንን ጉዳይ በከፋተኛ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ተበዳሪዎቹ የብድር ወለድ ስረዛና የተለያዩ የአገልግሎት ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡ የማሻሻያው ዋና ዓላማ እየተከሰተ ያለውን ችግር በጋራ ለመወጣት፣ በደንበኞች የንግድ እንቅሳቃሴ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ፣ የብድር አመላለስን የተሻለ ለማድረግና የአገራችን ኢኮኖሚ ሚዛናዊነቱን ጠብቆ ማስኬድ በሚቻልበት አካሄድ ባንኩ የራሱን ድርሻ ለመወጣት ታሳቢ በማድረግ ነው ፡፡
በዚህም መሰረት የእናት ባንክ የዳይሮክተሮች ቦርድና ማኔጅመንት በሚከተሉት ዝርዝር አገልግሎቶች ላይ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡
የብድር ወለድና አገልግሎት ክፍያን በተመለከተ
ባንኩ የኮረና ቫይረስ ደንበኞች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ከዚህ በታች ለተገለፁ ዘርፎች የብድር ወለድ ስረዛ፣ የአገልግሎት ክፋያና ቅጣቶች በጊዚያዊነት እንዲነሱ ወስኗል፡፡
- በሆቴልና ቱሪዝም የስራ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ደንበኞች ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ( እ.ኤ.አ ከሜይ 2020- ጁላይ 2020) የብድር ወለድ እንዳይከፍሉ ተሰርዟል፤
- ብድራቸውን ከሚጠበቅባቸው የመክፈያ ጊዜ ቀድመው ለሚከፋሉ ደንበኞች ይጣል የነበረው ቅጣት ሙሉ ለሙሉ ተነስ~ል፤
- የብደር ማራዘሚያ ላይ የሚከፈለዉ የአገልግሎት ዋጋ ሙሉ ለሙሉ ተነስ~ል፤
- የኦቨር ድራፍት እድሳት ላይ የሚከፈለዉ የአገልግሎት ዋጋ ተነስ~ል፤
- ውዝፍ የብድር እዳን አዘግይቶ ሲከፈል የሚጣል ቅጣት ተነስ~ል፤
- ከኮረና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አስቀድሞ በተቀመጠላቸው የብድር አከፋፈል ስርዓት ብድራቸውን መክፈል ለተቸገሩ ደንበኞች ተገቢዉ የብድር ግምገማ ከተደረገ በ=ላ የብደር መክፈያ ማራዘሚያ እየተደረገ ሲሆን በግምገማዉ ውጤትም ወለድን ጨምሮ ማራዘምና ተገቢዉ የእፎይታ ግዜ በመስጠት ደንበኞችን ከችግር የማውጣት ስራ እየተሰራ ነዉ
በአለምአቀፍ ባንኪንግ ዙሪያ
- አስመጪዎች እቃ ወደ ሃገር ለማስገባ ለከፈቱት ሌተር ኦፍ ክሬዲት (LC) አሁን በአለም ላይ ከተፈጠረዉ ችግር አኳያ አስቀድመዉ ለማራዘሚያ የሚጠየቁት የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ለሙሉ እንዲነሳ ተደርጓል
- እንዲሁም ከኮቪድ 19 ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ዕቃዎች ለሚያሰመጡ አስመጪዎች ባንኩ ሃምሳ ከመቶ (50%) የአገልግሎትና የኮሚሽን ክፍያ ቀንሷል፡፡
ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት በተመለከተ
እናት ባንክ ኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ለብሄራዊ የኮቪድ 19 ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የብር 2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን) ድጋፍ አበርክቷል፡፡
የባንኩን ሰራተኞችንና የቅርንጫፍ አገልግሎትን በተመለከተ
- እናት ባንክ ሰራተኞቹ ራሳቸውን ከኮቪድ 19 መጠበቅ እንዲያስችላቸው ለሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችና ለዋናው ቢሮ ሰራተኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፣ የእጅ ጓንት፣ ሳንቲሳይዘር፣ አልኮልና ፈሳሽ ሳሙና አቅርቦት አድርጓል፡፡
- በሁሉም ቅርንጫፎች የእጅ መታጠቢያ ስፍራ በማዘጋጀት ደንበኞች ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲስተናገዱ የሚያስችል የአሰራር ሂደት እንዲኖር ተደርጓል፡፡
- በተጨማሪም በዋናው ቢሮና በሁሉም ቅርንጫፎች ያሉ ሰራተኞች የባንኩን ስራ በማይጎዳ መልኩ በፈረቃ እንዲገቡ በማድረግ በተለይም ሁሉም ነፍሰጡር ሴቶች እቤታቸው እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡
- የኮቪድ-19 በተመለከተ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስራዎችን ለማጎልበት በባንኩ ቅርንጫፎች ቪዲዎች ተዘጋጅተው ደንበኞች ሊመለከቱት በሚያመች መልኩ በመተላለፍ ላይ ይገኛል፡፡
- እንዲሁም ከኮረና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ንክኪዎችን ለመቀነስ ደንበኞች ከኤ.ቲ. ኤም (ATM) ማሽኖች በክፍያ ካርድ በአንድ ቀን እስከ ብር 10, 000(አስር ሺ ) ድረስ ወጪ ማድረግ እንዲችሉ ተደርጓል፡፡
በአጠቃላይ እናት ባንክ እንደስሙ እናትነት ባህሪያትን በመላበስ ይህን ፈታኝ ወቅት ከደንበኞቹ፣ ከማህበረሰቡ ብሎም ከመንግስት ጋር በመደጋገፍ መታለፍ እንዳለበት በመገንዘብ ወደፊትም የተደረጉትን ማሻሻያዎች አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
//
//