News & Events

እናት ባንክ ለገበታ ለሀገር እና ለተማሪዎች ምገባ ፕሮጀክት ድጋፍ አደረገ

እናትነት ደግነትና መልካምነት ነው!!!

እናት ባንክ አ.ማ. የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ ብዙ ሥራዎች በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን@ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢፌድሪ  ጠቅላይ ሚኒስትሩር ዶ/ር አብይ አህመድ ይፋ የተደረገው በኦሮሚያ ወንጪ ሐይቅ፣ በአማራ ጎርጎራ እና በደቡብ ክልል ኮይሻ ለመስራት ለተቀረፀው የገበታ ለአገር ፕሮጀክት የብር 5 ሚሊዮን እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚማሩ የመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች  ምገባ ፕሮግራምና ለትምህርት ግብዓቶች ማሟያ የብር 1 ሚሊየን የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

Enat Bank launches Digital Banking Solution

PDF Embedder requires a url attribute

Addis Ababa, August 25, 2020- Enat Bank is pleased to announce the launches of All in one Digital Banking Services (Internet Banking, Mobile Banking and Mobile Wallet) to operate banking anywhere anytime at your fingertips.

The bank commences providing of these services starting from August 24, 2020 in all Addis Ababa branches. To translate one of its mission statements providing services with the state-of-the-art technologies, we fosters all in one Digital Banking Solutions via Internet Banking, Mobile Banking and Mobile Wallet services fittings to the demands of our customers.

These services allows our customers to access their bank and operate banking anywhere & anytime at their conveniences. The services include:

 • Transfer money between your own accounts,
 • Transfer money to other Enat Bank customers,
 • To effect payments like to reserve airline ticket, school fess,
 • To view Loan & advance and,
 • To view deposits and more.

Enat Bank stands to satisfy your banking needs at your convenience.

Enat Bank opened Sub branches

Enat Bank opened Sub-Branches in Diredawa and Mekele towns as of July, 2020. In our endeavor to create convenience, we are approaching to the door step of our esteemed customer. The bank is delighted to announce the opening of sub-branches in addition to the previously opened branches in Diredawa and Mekele towns respectively.

The Bank warmly invites residence, visitors or people working in and around its surrounding neighborhood of Diredawa and Mekele to pay visit to the sub-branches. Enat Bank well trained staff will be delighted to provide a personalized banking service catered to your financial needs.

Enat Bank stands to satisfy your banking needs.

Mane Ende Enat!

PDF Embedder requires a url attribute

Enat Bank amends Service fees

Description: LOGO.jpg

  ጋዜጣዊ መግለጫ

   እናት ባንክ ለተለያዩ የብድር ዘርፎች የብድር ወለድ ስረዛና የአገልግሎት ማሻሻያ አደረገ

ግንቦት 4, 2012 ዓ. ም – አዲስ አበባ ኢትዮጵያ፡ ኮረና ቫይረስ  በወረርሽኝነት በአለምአቀፍ ደረጃ መሰራጨት ከጀመረበት ወቅት አንስቶ በአለም ማህበረሰብ ላይ ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውሶችን በማድረስ ላይ ይገኛል ፡፡ በአገራችንም በተለይ በኢኮኖሚው ዘርፍ ይኸውም በአጠቃላይ የንግድ እንቅስቃሴውና በንግዱ ማህበረሰብ ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት በማድረስ ላይ ነው፡፡

እናት ባንክ ይህንን ጉዳይ በከፋተኛ ሁኔታ ከግንዛቤ በማስገባት  በተለያዩ የስራ ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ተበዳሪዎቹ የብድር ወለድ ስረዛና የተለያዩ የአገልግሎት ማሻሻያዎችን  አድርጓል፡፡ የማሻሻያው ዋና ዓላማ እየተከሰተ ያለውን ችግር በጋራ ለመወጣት፣  በደንበኞች የንግድ እንቅሳቃሴ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ፣ የብድር አመላለስን የተሻለ ለማድረግና የአገራችን  ኢኮኖሚ ሚዛናዊነቱን ጠብቆ ማስኬድ በሚቻልበት አካሄድ ባንኩ የራሱን ድርሻ ለመወጣት ታሳቢ በማድረግ ነው ፡፡

በዚህም መሰረት የእናት ባንክ የዳይሮክተሮች ቦርድና ማኔጅመንት በሚከተሉት ዝርዝር አገልግሎቶች ላይ ማሻሻያዎችን አድርጓል፡፡

የብድር ወለድና አገልግሎት ክፍያን በተመለከተ

ባንኩ የኮረና ቫይረስ ደንበኞች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀነስ ከዚህ በታች ለተገለፁ ዘርፎች የብድር ወለድ ስረዛ፣ የአገልግሎት ክፋያና ቅጣቶች  በጊዚያዊነት እንዲነሱ ወስኗል፡፡

 • በሆቴልና ቱሪዝም የስራ ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ደንበኞች ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ( እ.ኤ.አ ከሜይ 2020- ጁላይ 2020) የብድር ወለድ እንዳይከፍሉ ተሰርዟል፤
 • ብድራቸውን ከሚጠበቅባቸው የመክፈያ ጊዜ ቀድመው ለሚከፋሉ ደንበኞች ይጣል የነበረው ቅጣት ሙሉ ለሙሉ ተነስ~ል፤
 • የብደር ማራዘሚያ ላይ የሚከፈለዉ የአገልግሎት ዋጋ ሙሉ ለሙሉ ተነስ~ል፤
 • የኦቨር ድራፍት እድሳት ላይ የሚከፈለዉ የአገልግሎት ዋጋ ተነስ~ል፤
 • ውዝፍ የብድር እዳን አዘግይቶ ሲከፈል የሚጣል ቅጣት ተነስ~ል፤  
 • ከኮረና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አስቀድሞ በተቀመጠላቸው የብድር አከፋፈል ስርዓት ብድራቸውን መክፈል ለተቸገሩ ደንበኞች ተገቢዉ የብድር ግምገማ ከተደረገ በ=ላ የብደር መክፈያ ማራዘሚያ እየተደረገ ሲሆን በግምገማዉ ውጤትም ወለድን ጨምሮ ማራዘምና ተገቢዉ የእፎይታ ግዜ በመስጠት ደንበኞችን ከችግር የማውጣት ስራ እየተሰራ ነዉ

በአለምአቀፍ ባንኪንግ ዙሪያ  

 • አስመጪዎች እቃ ወደ ሃገር ለማስገባ ለከፈቱት ሌተር ኦፍ ክሬዲት (LC) አሁን በአለም ላይ ከተፈጠረዉ ችግር አኳያ አስቀድመዉ  ለማራዘሚያ የሚጠየቁት የአገልግሎት ክፍያ ሙሉ ለሙሉ እንዲነሳ ተደርጓል
 • እንዲሁም ከኮቪድ 19 ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ዕቃዎች ለሚያሰመጡ አስመጪዎች ባንኩ  ሃምሳ ከመቶ  (50%) የአገልግሎትና የኮሚሽን  ክፍያ ቀንሷል፡፡

ማህበራዊ ኃላፊነትን መወጣት በተመለከተ

እናት ባንክ ኮረና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ ለብሄራዊ የኮቪድ 19 ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ  የብር  2,000,000 (ሁለት ሚሊዮን) ድጋፍ አበርክቷል፡፡

የባንኩን ሰራተኞችንና የቅርንጫፍ አገልግሎትን በተመለከተ

 • እናት ባንክ ሰራተኞቹ ራሳቸውን ከኮቪድ 19 መጠበቅ እንዲያስችላቸው ለሁሉም ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶችና ለዋናው ቢሮ ሰራተኞች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ፣ የእጅ ጓንት፣ ሳንቲሳይዘር፣  አልኮልና ፈሳሽ ሳሙና አቅርቦት አድርጓል፡፡
 • በሁሉም ቅርንጫፎች የእጅ መታጠቢያ ስፍራ በማዘጋጀት ደንበኞች ርቀታቸውን ጠብቀው እንዲስተናገዱ የሚያስችል የአሰራር ሂደት እንዲኖር ተደርጓል፡፡
 • በተጨማሪም በዋናው ቢሮና በሁሉም ቅርንጫፎች  ያሉ ሰራተኞች የባንኩን ስራ በማይጎዳ መልኩ በፈረቃ እንዲገቡ በማድረግ በተለይም ሁሉም ነፍሰጡር ሴቶች እቤታቸው እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡
 • የኮቪድ-19 በተመለከተ  የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስራዎችን ለማጎልበት በባንኩ ቅርንጫፎች ቪዲዎች ተዘጋጅተው ደንበኞች ሊመለከቱት በሚያመች መልኩ በመተላለፍ ላይ ይገኛል፡፡
 • እንዲሁም ከኮረና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ንክኪዎችን ለመቀነስ ደንበኞች ከኤ.ቲ. ኤም (ATM)  ማሽኖች በክፍያ ካርድ  በአንድ ቀን እስከ ብር  10, 000(አስር ሺ ) ድረስ ወጪ ማድረግ እንዲችሉ ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ እናት ባንክ እንደስሙ እናትነት ባህሪያትን በመላበስ ይህን ፈታኝ ወቅት ከደንበኞቹ፣ ከማህበረሰቡ ብሎም ከመንግስት ጋር በመደጋገፍ መታለፍ እንዳለበት በመገንዘብ ወደፊትም የተደረጉትን ማሻሻያዎች አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

//

          

//

Enat bank S.C. donates ETB 2 million

Enat bank S.C. donates ETB 2 million

Enat bank S.C. donates ETB 2 million for the fight against #COVID19. The Bank delivers the donation to National Corona Virus Resource Mobilization committee at Ministry of Peace with the presence of the bank Board Chairperson W/o Hanna Tilahun and the President Ato Wondwossen Teshome  

እናት ባንክ ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ድጋፍ አደረገ

እናት ባንክ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡ የእናት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሀና ጥላሁንና የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ወንደወሰን ተሾመ በሰላም ሚኒስቴር ጽ/ቤት በመገኘት ለኮሮና ቫይረስ ብሔራዊ ሐብት አሰባሳቢ ኮሚቴ የገንዘብ ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

Find Us

Address

Kirkos sub-city, woreda 8, Jomo Kenyata Avenue, |Enat Tower |P. O. Box 18401, Addis Ababa, Ethiopia

Hours
Monday—Friday: 9:00AM–5:00PM
Saturday & Sunday: 11:00AM–3:00PM

CONTACT FORM

3 + 12 =

GET IN TOUCH

Kirkos sub-city, woreda 8, in front of Yordanos Hotel

info@enatbanksc.com

164278

+251 115 158278 / 507074

ENATETAA

Scroll Up

Pin It on Pinterest