+251 115 158278 info@enatbanksc.com

የእናት ባንክ የባለአክሲዮኖች  2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የተደረገ ጥሪ ማስታወቂያ

እናት ባንክ አ.ማ  በንግድ መዝገባ ቁጥር KK/AA/3/0006590/2006 የተመዘገበ ፣ የተፈረመ ካፒታሉ  ብዛት ብር 2,796,747,000 የሆነ ፣ ዋናው መስሪያ ቤት ቂርቆስ ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 8 በእናት ታወር ላይ የሚገኝ በንግድ ህግ ቁጥር 1243/2013 መሰረት 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ በኢንተር ሌግዠሪ ሆቴል አዳራሽ የሚካሄድ በመሆኑ፣ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸሁ አማካኝነት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በጉባኤው ላይ እንድትሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የ2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

1. ድምፅ ቆጣሪዎችን መሰየም፣

2. የጉባኤውን አጀንዳ ማፅደቅ፣

3. የባንኩ የካፒታል እድገት ውሳኔዎች መርምሮ ውሳኔ ማስተላለፍ፣

4. የባንኩን ካፒታል ማሳደግ፣

5. በአዲሱ ንግድ ህግ መሰረት የተሻሻለውን የባንኩን መመስረቻ ፅሑፍ ተወያይቶ ማፅደቅ፣

6. ቃለ ጉባኤውን ማፅደቅ፡፡

ማሳሰቢያ፡-

በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት ለማትችሉ ባለአክሲዮኖቸ ከስብሰባው እለት ሶስት ቀናት በፊት ካዛንቺስ የቀድሞው ዮርዳኖስ ሆቴል የአሁኑ መቅረዝ ሆስፒታል ፊት ለፊት እናት ታወር ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ፋይናንስና አካውንትስ መምሪያ በመቅረብ ባንኩ ባዘጋጀው የውክልና ቅጽ ላይ በመሙላት ተወካዮቻችሁን ማሳተፍ ትችላላችሁ % ወይም ተወካዮቻችሁ አግባብ ካለው የፌዴራል ወይም የክልል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተሰጠ በስብሰባ ለመሳተፍና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ይዘው በመቅረብ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡

ባለአክሲዮኖችም ሆናችሁ ወኪሎች ወደ ስብሰባው ቦታ ስትመጡ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ፤ እንዲሁም ተወካዮች የወካያችሁን የኢትዮጵያ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ  መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ በተጨማሪ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡

የእናት ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0115 58 28 35 /0115 50 70 74/0115 58 68 30 ይደውሉ፡፡