እናትነት ደግነትና መልካምነት ነው!!!
እናት ባንክ አ.ማ. የማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ ብዙ ሥራዎች በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን@ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩር ዶ/ር አብይ አህመድ ይፋ የተደረገው በኦሮሚያ ወንጪ ሐይቅ፣ በአማራ ጎርጎራ እና በደቡብ ክልል ኮይሻ ለመስራት ለተቀረፀው የገበታ ለአገር ፕሮጀክት የብር 5 ሚሊዮን እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2013 ዓ.ም በጀት ዓመት በከተማው ውስጥ ለሚማሩ የመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች ምገባ ፕሮግራምና ለትምህርት ግብዓቶች ማሟያ የብር 1 ሚሊየን የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡