እናት ባንክ አ.ማ በንግድ መዝገብ ቁጥር KK/AA/3/0006590/2006 የተመዘገበ ፣ የተፈረመ ካፒታሉ ብር 2,796,747,000.00 የሆነ ፣ የተከፈለ ካፒታል ብር 2,538,248,180.83፣ ዋናው መስሪያቤት ቂርቆስ ክ/ከተማ ፣ ወረዳ 8 በእናት ታወር ላይ የሚገኝ በንግድ ህግ ቁጥር 1243/2013 መሰረት 10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ አካባቢ በሚገኘው በሚሊኒየም አዳራሽ የሚካሄድ በመሆኑ ፣ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በጉባኤው ላይ እንድትሳተፉ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
10ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ
- ድምፅ ቆጣሪዎችን መሰየም፣
- የጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ፣
- የአክሲዮን ዝውውሮችን ማሳወቅ፣
- እ.ኤ.አ የ2022/2023 የባንኩን የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ረፖርት ማዳመጥ፣ መወያየትና፣
- የውጪ ኦዲተሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለጠቅላላ ጉባኤ ያቀረበውን ሪፖርት በተመለከተ ለጠቅላላ ጉባኤው አሰተያየት እንዲሰጥ በማድረግ ጉባኤው እንዲያፀድቀው መጠየቅ ፣
- እ.ኤ.አ የ2022/2023 የውጭ ኦዲተሮችን ሪፖርት ፣ የሀብትና እዳ ሚዛን እና ትርፍና ኪሳራ መግለጫ ማዳመጥ ፣ መወያየት እና ማíደቅ ፣
- እ.ኤ.አ ሰኔ 30 ቀን 2023 ስለተጠናቀቀው ሂሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ በቀረበው የውሳኔ ሃሳብ መሰረት መወያየትና ፣
- የዳይሬክተሮች ቦርድ ባቀረበው የትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የውጭ ኦዲተር ለጠቅላላ ጉባኤው አስተያየት እንዲሰጥ ማድረግና ጉባኤው እንዲያፀድቅ መጠየቅ፣
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እ.ኤ.አ የ2022/2023 የሂሳብ ዓመት የአገልግሎት ክፍያን እና እ.ኤ.አ የ2023/2024 ወርሃዊ አበል ክፍያን መወሰን ፣
- እ.ኤ.አ የ2023/2024 እስከ 2025/2026 የሶስት ዓመት የውጪ ኦዲተርን መምረጥና ክፍያን መወሰን፣
- የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን ፣
- የጠቅላላ ጉባኤውን ቃለጉባኤ ማíደቅ ናቸው ፡፡
ማሳሰቢያ፡-
በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት ለማትችሉ ባለአክሲዮኖቸ ከስብሰባው እለት ሶስት ቀናት በፊት ካዛንቺስ የቀድሞው ዮርዳኖስ ሆቴል ፊት ለፊት እናት ታወር ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ፋይናንስና አካውንትስ መምሪያ በመቅረብ ባንኩ ባዘጋጀው የውክልና ቅጽ ላይ በመሙላት ተወካዮቻችሁን ማሳተፍ ትችላላችሁ % ወይም ተወካዮቻችሁ አግባብ ካለው የፌዴራል ወይም የክልል የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተሰጠ በስብሰባ ለመሳተፍና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ከፒውን ይዘው በመቅረብ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡
ባለአክሲዮኖችም ሆናችሁ ወኪሎች ወደ ስብሰባው ቦታ ስትመጡ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ፤ እንዲሁም ተወካዮች የወካያችሁን ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ በተጨማሪ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡
የእናት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ 0115 58 28 35 /0115 50 70 74/0115 58 68 30 ይደውሉ፡፡