Back

የእናት ባንክ የባለአክሲዮች 12ኛ መደበኛና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ

marketing
5 min read

እናት ባንክ የባለአክሲዮች 12ኛ መደበኛና 3ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 11/2018ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ አካሂዷል።

ባንኩ በ2017ዓ.ም የሂሳብ በጀት አመት የአገልግሎት ተደራሽነቱን በማስፋት፣የፋይናንስ አካታችነቱን በማጠናከር ሴቶችን በኢኮኖሚ በማብቃት የተወዳዳሪነት ደረጃውን ከፍ ማድረግ ችሏል።

በሂሳብ በጀት አመቱ ተጨማሪ የሀብት አሰባሰብ ስራ በማከናወኑ የተቀማጭ ገንዘቡን ከፍ ማድረግ፣ጠቅላላ ሀብቱንና ትርፋማነቱን በማሳደግ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች እንደነበሩ ተገልጿል ።

ባንኩ 2017ዓም የሂሳብ በጀት አመት ካከናውናቸው ተግባራት መካከል የብሄራዊ ባንክ ለባንኮች ያስቀመጠውን የተከፈል ካፒታልን ለማሟላት የተሰራው ሰራ ተጠቃሸ ሲሆን፣በዚህም ባንካችን የተከፈለ ካፒታሉን ከ5ቢሊዮን ብር በላይ በማድረስ ከቀነ ገደቡ አስቀድሞ ማሟላት ችሏል።

እናት ባንክ በሚለዋወጠው ኢኮኖሚና የባንክ ስነ ምህዳር እድገቱን ለማፋጠን የሚያስችል ራዕይ ተኮር የስትራቴጂ ዕቅድን ተግባራዊ በማድረግ በትኩረት እየሰራ የሚገኝ ሲሆን፣ይህም የዲጂታል ፈጠራን፣ የደንበኞችን አገልግሎትን ማሳለጥ ፣ የባለአክስዮችን እሴት ማሳደግ የሚያስችል ነው።

Gallery