በርካታ ሴቶች የሥራ ዕድሉ አግኝተው ነገር ግን ዋስ/ተያዥ ባለማግኘታቸው ብቻ የዕድሉ ተጠቃሚ አይሆኑም። ይህንን ችግር ለመፍታት የፋይናንሺያል ዋስትና እንዲያገኙ ለማድረግ በእያንዳንዳቸው ስም በዝግ የባንክ አካውንት የተወሰነ ብር እንዲቀመጥና ዋስትና በማጣት የስራ እድል እንዳያመልጣቸው ያደርጋል፡፡ሙያተኞቹ አገልግሎት በሚሰጡበት ጊዜ ከጥንቃቄ ጉድለት በደንበኛው ንብረት ላይ የመሰበር ወይም የእምነት ማጉድል ችግሮች ቢፈጠሩ የህግ አካሄድን ተክትሎ መፍትሄ ያበጃል።በስምምነቱ መሰረትም ኢዚቲ የመረጃ አገልግሎት ኃ/የተ/የግል/ማ አገልግሎት ሰጪዎችን የመመልመል፣ የማሰልጠን እና ሥራ የማሰማራት ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡ በመሆኑም እናት ባንክ እንደስሙ እናት በመሆን ትኩረት ለተነፈገው ግን ለብዙዎች ፈታኝ ለሆነው ዋስ/ተያዥ የማጣት ችግር ዘላቂ መፍትሄ ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን ይዘን ብቅ ብለናል::እናት ባንክ ከተመሰረተበትና እየተገበረ ካለው የተሟላ የባንክ አገልግሎት አቅርቦት በተጓዳኝም ከሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት ማህበረሰብን የመጥቀም አካሔድ ወደፊትም ዘርፈ ብዙና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚጠቅሙና ችግር ፈቺ በሚሆኑ ስራዎች ላይ በስፋት አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Pin It on Pinterest

Share This