እናት ባንክ ከሃይብሪድ ዲዛይን ጋር በመተባበር የራይድ አሽከርካሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የብድር አገልግሎቶችን ለመስጠትና የተለያዩ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ባንካችን ያቀረባቸው የብድር ዓይነቶች እናት ራዕይ፣ እናት እፎይታ እና እናት ደራሽ የተሰኙ ናቸው።የአጋርነት ስምምነቱ አስፈላጊውን የፋናንስ የምክር አገልግሎት ማቅርብ፣ ለራይድ አሽከርካሪዎች የብድር አገልግሎት መስጠት፣ የተሳፋሪዎችን የክፍያ መንገድ ማቅለል እና ሌሎች አገልግሎቶችንም ያካትታል።

ስምምነቱ የእናት ባንክ ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤርሚያስ አንዳርጌ እና የሃይብሪድ ዲዛይን ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ሳምራዊት ፍቅሩን ጨምሮ ሌሎች ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት ተከናውኗል።

Pin It on Pinterest

Share This